ጀማሪ የኔትወርክና ሴኩሪቲ አስተዳዳሪ
Addis Capital Goods Finance Business S.C Addis Ababa · Addis Ababa Posted 16h ago
About this role
የስራ መስፈርቶች
የትምህርት ደረጃ: የመጀመሪያ ዲግሪ በኮምፒውተር ሳይንስ፣ ኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ ወይም በተመሳሳይ የትምህርት መስክ የተመረቀ/ቀች
የስራ ልምድ: 0 ዓመት
ብዛት: 1
ደመወዝ፡ 23761
ደረጃ፡ VII
የቅጥር ሁኔታ፡ በቋሚነት
የስራ ቦታ፡ አዲስ አበባ
ዋና ዋና ኃላፊነቶች
የድርጅቱን የኔትወርክ መሠረተ ልማት መቆጣጠርና ማስተዳደር
የኔትወርክ መሣሪያዎችን መጫን፣ ማዋቀር
የኔትወርክ ችግሮችን መለየትና መሠረታዊ የቴክኒክ ድጋፍ መስጠት
የኔትወርክና የሲስተም ደህንነትን መጠበቅ
ፋየርዎል (Firewall)፣ የተጠቃሚ መዳረሻ ፈቃዶችና የደህንነት መቆጣጠሪያዎችን ማስተዳደር
የኔትወርክ አፈጻጸምንና የደህንነት ሁኔታን በየጊዜው መከታተል
የማመልከቻ መመሪያ
አመልካቾች በትራንስክሪፕት የተደገፈ የትምህርት ማስረጃና ስርዝ ድልዝ ወይም ፍቀት የሌለው የስራ ልምድ ማስረጃቸውን ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ከየግል ሁኔታ መግለጫ ቅጽ (Curriculum vittae) ጋር በመያዝ አራዳ ጊዮርጊስ ደጃች ውቤ ቀይመስቀል ጀርባ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ህንፃ 4ኛ ፎቅ የሠው ኃይል ልማትና ሀብት አስተዳደር ቢሮ በመምጣት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ማስታወሻ፡ አመልካቾች የመውጫ ፈተና ማስረጃ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ከ2016 ዓ.ም እና ከዚህ በኋላ የተመረቁ ሆነው የትምህርት ማስረጃቸው በሚመለከተው አካል የተረጋገጠ መሆን ይኖርበታል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 0112179964 /0112179967 ይደውሉ፡፡
Never miss a role
New jobs land on Telegram first
Every opening we aggregate is posted to @ethio_tech_jobs within minutes — join the channel and be the first to apply.